የአዲሱ የKIA ቦርድ የመጀመሪያ ስብሰባ ተካሄደ!


የአዲሱ የKIA ቦርድ የመጀመሪያ ስብሰባ ተካሄደ!
አዲስ የተመረጠው የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ቦርድ የመጀመሪያ ስብሰባውን ትላንት፣ መስከረም 3/2019 ዓ.ም፣ በበይነመረብ አካሂዷል።
በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የተካሄደው ይህ የመጀመሪያ የቦርድ ስብሰባ፣ አዲስ የተመረጠው ቦርድ በቀጣይ የሥራ ዘመኑ የሚመራበትን ዓመታዊ የሥራ መርሐ ግብር በመወያየትና በማዘጋጀት ተጀምሯል።
በስብሰባውም ማህበሩ ባለፉት 4 ዓመታት ያሳለፈው ጉዞ፣ ያከናወናቸው ሥራዎችና ያስመዘገባቸው ውጤቶች በስፋት ተገምግመዋል። በግምገማውም የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ለማጠናከር እና በቀጣይ የሥራ ዘመን የበለጠ ውጤታማ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በተጨማሪም፣ በሚቀጥሉት 4 ዓመታት KIA ምን ደረጃ መድረስ እንዳለበት በጥልቀት በመመልከት፣ ከማህበሩ አመራር፣ ከኮንሶ ህዝብ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቁትን ውጤቶች መሠረት በማድረግ የማህበሩን ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማሻሻልና ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ አሰራሮችና የትግበራ ሥርዓቶች ላይ በተጨማሪ ውይይት ተደርጓል።
ይህም KIA ከዕቅድ ወደ ተግባር፣ ከሐሳብ ወደ ተጨባጭ ውጤት በመሸጋገር፣ በመሬት ላይ የሚታይ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎችን በተደራጀና በውጤታማ መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት የጣለ ስብሰባ ሆኗል።
በዚህ መሠረት KIA በሚቀጥሉት 4 ዓመታት የበለጠ የተደራጀ፣ ውጤታማ፣ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እና በኮንሶ ህዝብ ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ተቋም ለመሆን በትጋት ይሰራል።
ለአዲሱ የKIA ቦርድ የተሳካ የሥራ ዘመን እንመኛለን!


Comments