እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ!
እንቁ ለጣትሽ፣ እንቁ ለጣታችን!
ለመላው የኮንሶ ምሁራን ያለኝ መልዕክት
አዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ጉልበትና አዲስ የሥራ መነሳሳት ይዞ መጥቷል። ይህንን አዲስ ዓመት ስንቀበል የኮንሶ ምሁራን ሁሉ አንድ ላይ ቆመን፣ ተያይዘንና ተባብረን ለማኅበረሰባችን የሚጠቅም ሥራ እንሥራ።
ተያይዘን እንሥራ!
በአንድነት እንቁም!
በእውቀታችን ማኅበረሰባችንን እናግዝ!
ምሁራን በእውቀታቸው፣ በሙያቸውና በተሞክሯቸው ለማኅበረሰብ ትልቅ አቅም ናቸው። ይህን አቅም በተናጠል ሳይሆን በመተባበር ስናሰባስብ የምንፈጥረው ተፅዕኖ ከእያንዳንዳችን የተናጠል አቅም በላይ ይሆናል።
ተያይዘን ከሠራን፣ የሚወዱን የበለጠ ያከብሩናል፤ የሚጠሉንም ይፈሩናል። ለማኅበራችን ክፋት ያሰቡም የአንድነታችንንና የትብብራችንን ጥንካሬ በመመልከት ከክፉ ድርጊታቸው ይቆጠባሉ።
ይህ ማንንም ለመፍራት ወይም ለማስፈራራት ሳይሆን፣ አንድነት የሚፈጥረውን ኃይል ለመጠቀም፣ መተባበር የሚያመጣውን ውጤት ለማሳየትና ማኅበረሰባችንን በእውቀትና በተግባር ለማገልገል ነው።
እንግዲህ በዚህ አዲስ ዓመት ልዩነቶቻችንን አስቀምጠን፣ የሚያገናኙንን ነገሮች አጠናክረን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሥራ።
አንድ ምሁር ብዙ ሊያደርግ ይችላል፤ ተደራጅተው የሚሠሩ ምሁራን ግን ማኅበረሰብን ሊለውጡ ይችላሉ!
2019 ዓ.ም የኮንሶ ምሁራን የበለጠ የሚተባበሩበት፣ የሚደራጁበት፣ የሚያፈሩበትና ለሕዝባችን የሚጠቅም ተጨባጭ ሥራ የሚሠሩበት የተባረከ ዓመት ይሁንልን!
መልካም አዲስ ዓመት!
እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ!
ጉማቸው ኩሴ
የኮንሶ ምሁራን ማኅበር ሰብሳቢ



Comments