top of page
Search

#የትምህርት_ስብራትን_ለመጠገን_ከጥናት_እስከ_ተግባራዊ_ድጋፍ! #KIA

2 hours ago
1 min read

የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) የትምህርት ዘርፍን ለማጠናከርና በኮንሶ ዞን ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ያለመ ጥናታዊ ሥራ በማከናወን ከምርምር እስከ ተግባራዊ ድጋፍ የሚደርስ አስተዋጽኦ አበርክቷል።


ከነሐሴ 22–23/2018 ዓ.ም. በካራት ከተማ በተካሄደው 4ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ወቅት፣ ማህበሩ በኮንሶ ዞን የትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት ያለመ ጥናታዊ ጽሑፍ አዘጋጅቶ በማህበሩ የጥናትና ምርምር ቡድን ሰብሳቢ ዶ/ር ሲቢሎ ጋሹሬ አማካኝነት ለጉባኤው አቅርቧል። የጥናቱ አቀራረብ በትምህርት ዘርፉ ያሉ ችግሮችን በጥናትና በማስረጃ በመለየት፣ ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመፈለግ ያለውን የማህበሩን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።


ከዚህም በተጨማሪ፣ ማህበሩ በዚያው ጉባኤ ወቅት በኮንሶ ዞን ለሚገኙ አቅመ ደካማ ተማሪዎች የሚውል የደብተርና የጽሕፈት መሣሪያዎች ድጋፍ ለኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስረክቧል።


1. #ደብተር = 78 ደርዘን እና ተጨማሪ 10 ደብተሮች፣ ባለ 50 ገጽ።

2. #ስክሪብቶ፦ 3 ፓኬት እና 1 ፍሬ።

3. #እርሳስ፦ 6 ፓኬት።


ይህ ተግባር የኮንሶ ምሁራን ማህበር የትምህርት ችግሮችን በጥናት ለመለየት፣ መፍትሔዎችን ለማመላከትና በተግባርም ለመደገፍ ያለውን አቋም ያሳያል። ዘላቂ የትምህርት ለውጥ ለማምጣት የጥናት፣ የተቋማት ትብብር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና የተማሪዎች ድጋፍ በአንድነት መጓዝ ያስፈልጋል።


የኮንሶ ምሁራን ማህበር በምርምር፣ በአቅም ግንባታና በማህበራዊ ተሳትፎ ለኮንሶ ህዝብ ዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ያስቀጥላል።


ኮንሶ ምሁራን ለኮንሶ ህዝብ እድገት!


 
 
 

Comments


bottom of page