የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከኮንሶ ዞንጨሠገን ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።
- basire balcha
- 2 days ago
- 1 min read










የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከኮንሶ ዞንጨሠገን ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።
በሥልጠና መድረኩ ላይ "የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset)"፣ "የስሜት ልህቀት"፣ "የሥራ ሥነ-ምግባር" እና "የአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለባለሙያዎች ጥልቅ ሥልጠና ተሰጥቷል።
በማጠቃለያው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሠገን ዙሪያ ወረዳ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ አለምገና አያኖ፤ "የተለወጠ አእምሮ ለፈጠራና ለሥራ ሁልጊዜ ዝግጁ ነው" ብለዋል። ባለሙያውም ከሥልጠናው ያገኘውን ዕውቀት በመጠቀም ለማኅበረሰቡ ለውጥ የሚተጋ መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።
አቶ አለምገና አክለውም፣ ባለሙያዎች ሥልጠናውን ወደ ተግባር በመቀየር ለሕዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸው፤ ሥልጠናውን ላዘጋጀው የኪያ (KIA) ማኅበርና ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለተከታተሉ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
የሥራ ሥነ-ምግባር ሰነድን ያቀረቡት የወረዳው የኪያ ማኅበር ሰብሳቢ አቶ ጀምስ ኮርጋሌ በበኩላቸው፤ ሠልጣኞች ከሥልጠናው በኋላ በተመደቡበት የሥራ መስክ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደሚገባቸው አስረድተዋል። ተገልጋዮችን በተገቢው መንገድ ማስተናገድና በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጸ የአገልጋይነት ስሜትን መላበስ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኮንሶ ምሁራን ማኅበር አባልና የኮንሶ ዞን የሥራና ክህሎት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጌታሁን ገመቹ "የስሜት ልህቀትና የአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ሰነድ፤ የስሜት ልህቀት በአስተሳሰብ ደረጃ አርቆ ለማሰብና አዳዲስ ሐሳቦችን ለማመንጨት ያለውን ፋይዳ በዝርዝር አስገንዝበዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፤ ሥልጠናው እጅግ ወሳኝና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ዘመኑን የዋጀ፣ በአመለካከት የተለወጠ፣ በቡድን የመሥራት ፍላጎቱ የዳበረ፣ በሥነ-ምግባር የታነጸና ለተገልጋይ ልዩ ክብር በመስጠት ቀልጣፋ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።


Comments