የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከኮንሶ ዞን የሠገን ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለወረዳው ሲቪል ሰርቫንቶች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል
- basire balcha
- 4 days ago
- 1 min read





የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከኮንሶ ዞን የሠገን ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለወረዳው ሲቪል ሰርቫንቶች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።
በህዝብ አገልጋይ የአስተሳሰብ ቅኝት (Glocal mind set for public servant)፣ በሥራ ስነምግባር እና ሙያዊነት ( Work Ethics and Professionalism)፣ በህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ( Public Service delivery) እና በስሜት ልህቀት (Emotional Intelligence) በሚሉ ርዕሶች ለወረዳው የህዝብ አገልጋዮች ለ2 ቀን የምቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ሥልጠናውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ በራቆ በንግግር የከፈቱት ሲሆን፣ ማህበሩ የአካባቢውን የልማት ችግሮች በጥናት ለመፍታትና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚሠራ "ከእኛ በእኛ ለእኛው" የተመሠረተ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።
ምሁራን ባላቸው ዕውቀት ማህበረሰቡን በቅንነትና በፍጥነት እንዲያገለግሉ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ሥልጠና፣ በዶክተር ኩሴ ጋሮ መሪነት እየተሰጠ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
ባሳለፍነው ሳምንት ተመሳሳይ ሥልጠና በኮልሜ ወረዳና ካራት ከተማ አስተዳደር መሰጠቱ ይታወሳል።


Comments