የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከከና ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ።
- basire balcha
- 3 days ago
- 1 min read






የኮንሶ ምሁራን ማህበር (KIA) ከከና ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ።
በሥልጠና መድረኩ ላይ በ"አስተሳሰብ ለውጥ (Mindset)"፣ "በስሜት ልህቀት"፣ "በሥራ ሥነ-ምግባር" እና "በአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት" ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
የከና ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ዘርፉ ላቄው በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፤ ሥልጠናው ለወረዳው ሠራተኞች እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በቀጣይ በሰፊው የሚሰጥበት ዕድል እንደሚመቻች ተስፋ ሰጥተዋል።
የማህበሩ አባልና አሰልጣኝ እጩ ዶ/ር ሳሙኤል በርሻ እንደገለጹት፤ የሥልጠናው ዋና ዓላማ የመንግሥት ሠራተኛው ለችግሮች መፍትሔ ለመፈለግ ከአካባቢያዊ አስተሳሰብ ወጥቶ ዓለምአቀፋዊ ዕይታ እንዲኖረውና የመፍትሔ አካል እንዲሆን ማስቻል ነው።
ሌላኛው የማህበሩ አባልና አሰልጣኝ መምህር ጋሻው ገያቦ በበኩላቸው፤ ሥልጠናው ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁና በሥራ ሥነ-ምግባር የታነጸ ስብዕና ያለው ትውልድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስታውሰዋል።
የመድረኩ አመቻች አቶ ኩኛ ኩንጫርታ፤ ሠልጣኞች ከሥልጠናው በኋላ የአዕምሮና የሥነ-ምግባር ለውጥ ለማምጣት ዘወትር ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሥልጠናው በእጅጉ እንደሚረዳ እምነታቸውን ገልጸዋል።


የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፤ ሥልጠናው ወሳኝና ወቅታዊ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል።


Comments